የተጨማሪ እሴት ታክሱ የሚመለከተው ከአንድ ቤተሰብ ወርሃዊ አማካይ ፍጆታ በላይ ኤሌክትሪክ እና ውሃን በብዛት የሚጠቀመው የመክፈል አቅም ያለው የህብረተሰብ ክፍል ነው ተብሏል፡፡
መንግስት አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል በመኖሪያ ቤቱ የሚጠቀመውን አማካይ ወርሃዊ የውሃና ኤሌክትሪክ ፍጆታ ከታክሱ ነፃ የሚያደርግ ሲሆን ከታክሱ ነፃ ከተደረገው በላይ የውሃና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተፈፃሚ እንዲሆን ያደርጋል ተብሏል፡፡
በተመሳሳይ የትራንስፖርት አገልግሎትም ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፍሉት ባለሦስት እግር ተሽከርካሪን ሳይጨምር፣ አሽከርካሪውን ጨምሮ ከስምንት ሰው በታች የመጫን አቅም ያላቸውን ተሽከርካሪዎች በመጠቀም የሚሰጥ የትራንስፖርት አገልግሎት መሆናቸው ተገልጻል፡፡
ሚኒስቴሩም የትራንስፖርት አገልግሎትም ላለፉት 22 ዓመታት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ እንዲሆን የተደረገው አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ለትራንስፖርት የሚያወጣው ወጪ እንዳይንር እንዲሁም በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚከፈለው ታክስ የዕቃዎችን ዋጋ መናር እንዳያስከትል በማሰብ ነበር ብሏል፡፡
በመሆኑም ከህዝብ እና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ውጪ ለሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች የዚህ አይነቱን ድጋፍ ማድረግ ተገቢ ባለመሆኑ፣ መንግስት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የመሆን መብት ባለሶስት እግር ተሽከርካሪን ሳይጨምር ከስምንት መቀመጫ በላይ ያላቸው ተሸከርካሪዎች መሆኑ…