አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
#Ethiopia | የበረራ ደህንነትን የሚጥሱ ደንበኞች በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ህግ ተጠያቂ ይሆናሉ ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ።
አቶ መስፍን እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኛ ንጉስ ነው ብሎ የሚያምንና ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ህግን አክብሮ የሚሰራ ተቋም ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ ባጋጠመው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ በሀገር ውስጥ የበረራ መርሐ-ግብር ወደ መቀሌ ተጉዘው የነበሩ ሁለት አውሮፕላኖች ማረፍ ሳይችሉ ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን አስታውሰዋል፡፡
ሌላ ወደ መቀሌ ለመብረር በዝግጅት ላይ የነበረው አውሮፕላን የአየር ሁኔታው ለደኅንነት አስጊ በመሆኑ መብረር አልቻልም። በመሆኑም ተጓዦች ወደ ተርሚናል ውረዱና የሚሆነውን ነገር እንነግራችኋለን ሲባሉ “አንወርድም፤ መሄድ አለብን፤ አውሮፕላኑ ይከስከስ” ሲሉ የነበሩ ያሉ አንዳንድ ደንበኞች በህግ እንደሚጠየቁ አስታውቀዋል።
አየር መንገዱ የአገልግሎት ጥራት ደረጃን በማውጣት ደንበኞችን በአገልግሎት አሰጣጥ የማርካት፣ እያንዳንዱ አውሮፕላን በተመደበለት ስዓት እንዲወጣ የማድረግ፣ የደንበኞች ሻንጣ ጉዳት ሳይደርስበት ከደንበኞች ጋር እኩል እንድሄድ የማድረግና ሌሎች በርካታ ስራዎችን መስራቱን አስታውቀዋል።
የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት በየጊዜው በመገምገም ደንበኞችን ለማርካት እየሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።
በሄለን ወንድምነው