ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ
“የእልል ያልኩ ሐበሻ” የብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተመረጠ
#Ethiopia | ወጣቱ ድምፂዊ የሀበሻን ባህላዊ እሴቶችን እንዲሁም ሐበሻ ቢራን እንዲያስተዋውቅ የተመረጠው በሐበሻ ቢራ ፉብሪካ ነው።
በአንድ አልበም እና በተለያዮ ነጠላ ዜማዎች ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ብራንድ አምባሳደር ሆኖ በመመረጡ የሀበሻ መገለጫ የሆኑ እሴቶች በዓለም አደባባይ ጎልተው እንዲወጡ ይሰራል።
“እልል ያልኩ ሀበሻ ” በሐበሻ ቢራ አዘጋጅነት የደመቀ ዝግጅት ተካሄዷል።
በቃና ዌርሀውስ በተዘጋጀው በአይነቱ ለየት ያለ ፐሮግራም የኢትዮያዊያን ባሀል፤ ዕሴት፤ማንነት እና ወግ በተለያዩ ክዋኔዎች ባህላዊውን ከዘመነኛው ጋር ያሰናሰኑ ዝግጅቶች ቀርበዋል።
በዚህም በምግብ አዘገጃጀት፤በፋሽን ትርዒት፤ በሙዚቃ እና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ባሀላዊው ከዘመናዊ ጋር በማሠናሠል ስራ የበረቱ ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።
የዝግጅቱ ዓላማም የሀበሻ መገለጫ የሆኑ አለባበሰ፣ምግብ ዝግጅት ፣ሙዚቃ እና የመሳሰሉትን በተለያዩ ሀገረኛ መድረኮች ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቁ ማድረግ እና እነዚህን ሁነቶች ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ጎን ለጎን እራሳቸውንም እንዲያስተዋውቁ መደገፍ ነው።