#Ethiopia | የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም አርፈዋል።
የፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ አጭር ታሪክ
ፕሮፌሰሩ ‹‹ በልጅነቴ በጣም የታደልኩ ነበርኩ፡፡ ሶስት ቤተሰቦች ናቸው ያሳደጉኝ ማለት እችላለው ይላሉ ›› በገዛ አንደበታቸው ስለ ራሳቸው ሲናገሩ፡፡ የፕሮፌሰሩ ታሪክ ከዚህ ይጀምራል፡፡
የዛሬው ፕሮፌሰር አንድሪያስ እሸቴ ከወላጅ እናታቸው መንበረ ገብረ ማርያም እና ከወላጅ አባታቸው ከእሸቴ ተሰማ ተወልደው በመሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ልጅነታቸውን አሳልፈዋል፡፡
ከእናት እና አባታቸው በመቀጠል ያሳደጓቸው አጎታቸው ጀማነው አላብሰው ወጣትነታቸውን ደግሞ በፓንክረስት ቤተሰቦች ውስጥ እንደ ልጅ በመሆን ትምህርታቸውን እየተከታተሉ በእንክብካቤና በንባብ ራሳቸውን በእውቀትና በልምድ ማጎልበት ችለዋል፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ የዘመናዊ ትምህርት ቤት ፋናወጊ በመሆን በሚጠቀሰው ዳግማዊ ምንሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ህይወታቸውን ብለው የጀመሩት የያኔው አንድሪያስ እሸቴ በዊልያምስ ኮሌጅ ትምህርታቸውን ተከታትለው ከየል ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እስካገኙበት ጊዜ ድረስ ሰፊ የንባብ ልምድና የፍልስፍና ሕይወት ውስጥ አልፈው ከሀገር ውጪ በተለያዩ ቦታዎች ከሰሩና በበርካታ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ካስተማሩ በኋላ ወደ ሀገር ውስጥ በመመለስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት በመሆን አገልግለው ቀጥለውም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡ በ1995ዓም የኢትዮጵያ ህገ መንግስት…