በዓለ እረፍቱ ሐምሌ 15 የሚታሰበው ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ውዳሴ የደረሰው አባት ነው፡፡ ለእመቤታችን ካለው ፍቅር የተነሳ የእመቤታችን ምስጋናዋ በዝቶልኝ እንደ እንጀራ ተመግቤው እንደ ውሃ ጠጥቼው ሲል ይመኝ ነበር፡፡ ሲጸልይም እመቤታችን በምድር ላይ በኖረችበት እድሜ ልክም በየቀኑ 64 ጊዜ ይጸልይ ነበር፡፡
የገዳማውያን አባቶች ሀሳብም ይኸው ነው፣ እዚህ በስጋ ገበያ ስንሮጥ ነፍሳችንን ለረሳነውና ለመላው ዓለም ድህነትና ምህረት መጸለይ፡፡ ይህ እንዲሆን ግን ምቹም ባይሆን ጸሎታቸውን እንዲቃያቋርጡ፣ እንዲሰደዱ ከሚያደርግ ሁኔታ የተሻለ ማረፊያ ቦታ ይሻሉ፡፡
ቅዱስ ኤፍሬም ታዲያ አንድ ቀን “ለነግህ” ለማለዳ ጸሎቱ በተነሳበት እምቤታችን መጥታ መንፈስ ቅዱስ በገለጸልህ መጠን አመስግነኝ በማለት በሰባቱ ቀናት የምትመሰገንበትን ውዳሴ ማርያም ጨምሮ ሕልቆ መሳፍርት የሌለው ምስጋና የደረሰበትን ጥበብ ልጇ ወዳጇ የተመኘውን እንዲሰጠው አድርጋለች፡፡ ከብዛቱ የተነሳ መቋቋም ተስኖት “አቤቱ የጸጋህን ሞገድ ያዝልኝ” እስኪል ድረስ፡፡
የኛ ገዳማውያን አባቶችስ እንደ ቅዱስ ኤፍሬም ዘወትር ሀሳባቸው ጸሎትና ወደ እግዚአብሔር መመልከት እንዲሆን፣ በአታቸው እንዳይፈታ ምን ያህል እያገዝናቸው ነው?
ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለተጨማሪ መረጃ:-
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957
ወይም 0938644444