ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታ
የዓመቱ የሰብል ልማት ተመራማሪ ተብለው ተመረጡ
#Ethiopia | የአሜሪካው ስመጥር ፑርዱ ዩኒቨርሲቲ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ፕሮፌሰር ገቢሳ ኤጀታን በአከናወኑት የግብርና ምርምር ሥራ የዓመቱ የሰብል ልማት ተመራማሪ አድርጎ መርጧል፡፡
በተለያየ ጊዜ በአካሄዱት ምርምር “ሃይብሪድ” የሆኑ የማሽላ ዘሮችን መፍጠር የቻሉ አንጋፋ ምሁር ሲሆኑ፣ በዚህ ለወገን ጠቃሚ ተግባራቸውም በዘርፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና የተቸራቸው ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡