ተዋናይት ፍናን የኢንፊኒክስ የብራንድ አምባሳደር ኾና ተሾመች#Ethiopia | ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ ታዋቂዋን ተዋናይ ፍናን ሂ…

ተዋናይት ፍናን የኢንፊኒክስ የብራንድ አምባሳደር ኾና ተሾመች

#Ethiopia | ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ ታዋቂዋን ተዋናይ ፍናን ሂድሩን የብራንድ አምባሳደር በማድረግ አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

ኢንፊኒክስ ኢትዮጵያ ታዋቂዋን አከተር ፈናን ሂድሩን የብራንድ አምባሳደር በማድረግ አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡ የአብሮ መስራት ስምምነቱ የአንድ አመት ቆይታ የሚኖረው ሲሆን ፍናን ክብራንዱ ጋር በቅርበት በመስራት በተለይም ወጣቱን ከብራንዱ ጋር በማስተዋወቅ የራሷን ድርሻ ትወጣለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፍናን በፊልሙ ኢንደስትሪ በተለይም በወጣቱ ዘንድ ያሳየችውን ተቀባይነት እና ያላት የፈጠራ ችሎታ ከኢንፊኒክስ ብራንድ ጋር አብሮ ለመስራት ምቹ የሚያደርገው ሲሆን ኢንፈኒከስ ከሚታወቅበት የስልክ ገበያ በተጨማሪ ወደ ቲቪ፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ኤር ፖድ እና መሰል ምርቶችን ወደ ገበያው ለማቅረብ ያለውን አላማ በመደገፍ ረገድ ጉልህ ተሳትፎ ይኖራታል።

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ሁነቱ ላይ የተገኙት የኢኒፊኒክስ ኢትዮጵያ ብራንድ ማናጀር አቶ አሌከስ ” ከታዋቂዋ አከተር ፍናን ሂድሩ ጋር አብረን ለመስራት በመቻላችን ድስተኛ ነን” ያሉ ሲሆን “ፈናን ወጣቱን እና አዳዲስ ፈጠራን በመወከል ኢንፈኒከስ ብራንድ በወጣቱ እና በመላው የህብረተሰብ ከፍል በሚገባው ደረጃ እንዲታወቅ ሰፊ ድርሻ ይኖራታል ብለን እናስባለን” ብለዋል፡፡

ፍናን በበኩሏ ” ከዚህ ትልቅ ብራንድ ጋር አብሮ ለመስራት በመቻሌ አጅግ ደስተኛ ነኝ” ያለች ሲሆን “በአብሮነት ጉዞዎችን ተጠቃሚውን ከብራንዱ ጋር በማስተዋወቅ እና ከኢንፊኒክስ ምርቶች ጋር በማገናኘት የሚጠበቅብኝን ለመወጣት እሰራለሁ” ብላለች።

ኢንፊኒከስ አለም አቀፍ የኤሌከትሮኒከስ አምራች ኩባንያ ሲሆን በተለይም…

Search News

All News Categories

Stay In Touch

Abbay TV Entertainment

Abbay TV News

Abbay TV Entertainment

Abbay TV News

© Abbay TV. All rights reserved.