#Ethiopia | አሸባሪ ቡድኖች ላይ የተገኘውን ውጤት አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን ኢትዮጵያ እንደማትታገስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወቅታዊ ቀጣናዊ ጉዳይ ላይ ማምሻውን በአወጣው መግለጫ÷ ኢትዮጵያ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ከሶማሊያ ሕዝብ እና ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር በመሆን በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን ለመከላከል አሁንም ቁርጠኛ አቋም አላት ብሏል፡፡
ሚኒስቴሩ ያወጣው መግለጫው ሙሉ ቃል ቀጥሎ ቀርቧል፡-
***
በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የተሰጠ መግለጫ
በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) በቀጣይ የሚኖረው አዲስ የሰላም ተልዕኮ አወቃቀር ሁኔታ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ላይ አዲስ ስጋት ይዞ መምጣቱ ኢትዮጵያን የሚያሳስብ ሆኗል፡፡
የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለዚሁ አዲስ ሽግግር እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ቀጣናው ሊተነበይ ወደማይቻል ፈተና ውስጥ እየገባ ይገኛል፡፡
በሁኔታው ላይ ቀደም ሲል ኢትዮጵያን ጨምሮ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ውስጥ ወታደር ያዋጡ አገሮች ተደጋጋሚ ጥሪዎችና አስተያየቶች ትኩረት አልተሰጣቸውም፡፡
የመከላከያ ሠራዊታችንን መልካም ስምና ዝናን እንዲሁም መስዋዕትነት የሚያጠለሹ ተከታታይ መግለጫዎች ሲወጡ ኢትዮጵያ በዝምታ እንድታልፍ ከአንዳንድ ወገኖች በኩል ፍላጐት መኖሩ ይታያል፡፡
ሌሎች ተዋናዮች የአፍሪካ ቀንድ ክልልን ለማተራመስ እርምጃ ሲወስዱ ኢትዮጵያ በዝምታ አትመለከትም፡፡
ይህም በመሆኑ በቀጣናው የብሄራዊ ደህንነቷን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን ሁሉ በንቃት እየተከታተለች ትገኛለች፡፡…