#Ethiopia | በጋሞ ዞን ዲታ ወረዳ የግብረስጋ ድፍረት በደል የፈጸመው ተከሳሽ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተወስኗል።
ተከሳሽ አቶ ቱካ ቱጋሞ ዕድሜ 45 ስሆን በ1996ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 627(5) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የዲታ ወረዳ አቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፡፡
የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ የግብረስጋ ግንኙነት በመፈጸሙ ነሀሴ 5/ 2016ዓ.ም ዕሁድ ከቀኑ 9:00 የሚሆንበት ጊዜ በዲታ ወረዳ ዛዳ ከተማ ቀበሌ ልዩ መጠሪያው ሚሽዳ ቀጠና ተብሎ የሚጠራበት አከባቢ የ3አመት ልጅ የሆነችውን የግል ተበዳይ
ህፃን ብርቱ ገነነ ዕድሜ ሦስት ዓመት የሆነችው ልጅ ከሌሎች ልጆች ጋር ከብቶችን በሚያግዱበት ቦታ ተከሳሽ አንቀላፍታለች በማለት አቅፎ ወደ ተበዳይ ወላጅ አባቷ ቤት ድረስ በማምጣት አስገድዶ በመድፈር የከባድ አካል እና ሥነ ልቦና ጉዳት ያደረሰባት በመሆኑ የፈፀመው በህፃን ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረስጋ ድፍረት ወንጀል ክስ አቅርቧል።
ዐቃቤ ህግ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያስረዱልኛል ያላቸውን ዝርዝር የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያሰረዳ ሲሆን ተከሳሽም ወንጀሉን ስላለመፈጸሙ ማስረጃ አቅርቦ ያላሰተባበለ በመሆኑ ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ህግን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መሰረት በማድረግ ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት ነሀሴ 22/2016 ዓ.ም በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እዲቀጣ ተወስኖበታል ፡፡
የዲታ ወረዳ መ/ኮሚዩኒኬሽን