ውይይቱን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የመሩት ሲሆን፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃርም በውይይቱ ተገኝተዋል።
ኢንጂነር ታከለ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
ይህንን እውነታ በመረዳት ከአንድ ክፍለ ዘመን ባሻገር የቆዩ የሀገር መሪዎች የጥንቱን ባቡር ዕውን በማድረግ ኃላፊነቱን ጭምር ለአሁኑ ትውልድ አስረክበዋል ብለዋል።
ላለፉት ስድስት ዓመታት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር የሚጠበቅበትን ሀገራዊ አበርክቶ ከማምጣት ይልቅ በተለያዩ ምክንያቶች ለዕዳ ሲዳረግ መቆየቱን ጠቁመዋል።
አክሲዮን ማህበሩ ከዕዳ ወደ ትርፋማነት በመለወጥ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ሚና እንዲወጣ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አመልክተዋል።
በሁለት ወዳጅ ሀገራት የተመሠረተው አክሲዮን ማህበሩ ታላቅ ራዕይ የሰነቀ የንግድ ተቋም መሆኑን ጠቁመው፤ ተቋሙን ወደ ለውጥ ጎዳና ለማምጣት ሠራተኛ እና አመራሩ በተናበበ መንገድ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
የተጀመረውን ለውጥ ለማሳካት የሚያግዙ የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድና የተናበበ ስራ መስራት የሚያስችል አደረጃጀት መዘጋጁትንም አውስተዋል።
በእነዚህ የአሠራርና የአደረጃጀት መንገዶች እና ስትራቴጂክ ዕቅድ በመታገዝ በሶስት ዓመታት…