ትኩረት የተነፈጋቸው የዳሰነች ነዋሪዎች!
#Ethiopia | ከተፈጥሮ ጋር ታግሎ፣ተሳማምቶ እና በፈጣሪ ተማምኖ የሚኖር ማህበረሰብ ነዉ። ያለዉን ለመስጠት፣እንግዳ ለመቀበል ሰንፎ አያዉቅም። የሚሰማዉን ፊት ለፊት የሚናገር፣ቂም መያዝን አያዉቅም። በፈገግታ ተቀብሎ በምርቃት ምራቅ እንትፍ ብሎ የሚሸኝ የዋህ፣የድንበር ዘብ ሀገር ጠባቂ ህዝብ ነዉ የደቡብ ኦሞዉ የዳሰነች ወረዳ ነዋሪ ኛንጋቶሞ ማህበረሰብ።
ያ የዋህ ህዝብ ዛሬ የሚደርስለትን እየተማፀነ ነዉ። ኦሞ ወንዝ ከወትሮው በተለየ የጨከነባቸዉ ይመስላል።እንደ ልጆቻቸው የሚያዩአቸው ከብቶች በጎርፍ ተወስደዋል። ደሳሳ ጎጆአቸዉ በዉሃ ተጥለቅልቋል። እናም ያ የሚተማመኑት ፈጣሪ እንዲደርስላቸው፣ ኢትዮጵያዉያን እጃቸውን እንዲዘረጉ ድምፅ ሆነው ድምፃቸውን እንዲያሰሙላቸዉ ይሻሉ።
ያ ከሰዉ ፊት መቆም የማይወድ ፣የሰዉ እጅ የማያይ፣ በረጅም መፋቂያ ነጭ ጥርሱን እየፋቀ ከከብቶቹ ጋር የሚንጎራደደዉ ማህበረሰብ ዛሬ ሁሉም ነገር ጨልሞበታል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት ተመሰቃቅሏል።ደራሽ ወገን፣ፈጣን መንግስታዊ ምላሽ ይሻሉ።ለምን ትኩረት ተነፈግን ብለዉ ይጠይቃሉ።
ድምፅም ድጋፍም እንሁናቸው?
(ደስታ አባዲ)